የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ልዑክ ለወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ሥራና የእርስ በእርስ ግንኙነት ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ታርጫ ከተማ ገቡ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) “በጎነት ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ልዑክ ለወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ሥራና የእርስ በእርስ ግንኙነት ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ታርጫ ከተማ ገብተዋል፡፡
ልዑኩ ታርጫ ከተማ ሲደርስ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዐቢይ አደሞን ጨምሮ የክልልና ዳዉሮ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ያነገበዉን የወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴት በወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች የበጎ ስራና የእርስ በእርስ ግንኙነት ማጠናከር የቡድኑ ዓላማ እንደሆነም ነው የተገለጸው።
በሀገር ደረጃ ለሚገነባው የገዢ ትርክት እሳቤና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር የወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ሥራና የርስ በእርስ ግንኙነት ወሳኝ መሆኑም ተገልጿል።
የክልሉ ወጣቶች ክንፍ አመራር አባላት በከተማው በሚኖራቸው ቆይታ የልማት ሥራዎች ጉብኝት፣ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላና የበጎ ስራዎች እንደሚያከናውኑ ይጠበቃል።
በመርሃ ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ አመራሮች፣ የ12ቱም ዞኖችና የ3ቱ ሪጂዮ ፖሊስ ከተሞች የወጣቶች ክንፍ አመራሮች ተገኝቷል።
ዘጋቢ፡ መሳይ መሠለ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
የቡርጂ ዞን ምክር ቤት አቶ ትንሳኤ ዮሐንስ ወጌ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ
የወባ በሽታ ስርጭትን የመከላከልና የመቆጣጠርን ጉዳይ ቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየሰራ መሆኑን የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ
አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ተገልጋዩን ለማርካት እየሰራ መሆኑን የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ