የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ልማት ለማጠናከር አንድነት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ልማት ለማጠናከር አንድነት ወሳኝ መሆኑን የልዩ ወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪና የጠምባሮ ልማት ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር ሀብታሙ በላይነህ ገለፁ፡፡
በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማና አከባቢ ከሚኖሩ የጠምባሮ ተወላጆችና አጋሮች ጋር የጠምባሮ ልማት ማህበርን ለማጠናከር የምክክር መድረክ በዱራሜ ከተማ እየተካሄደ ነዉ፡፡
የጠምባሮ ልማት ማህበር ባለፈዉ ዓመት ግንቦት ወር በይፋ ተመስርቶ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የገለፁት የልዩ ወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ሀብታሙ በላይነህ፥ የልማት ማህበሩን የቦርድ አመራር በመምረጥና ስትራቴጂክ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር መግባቱን ተናረዋል፡፡
ልማት ማህበሩ በትምህት፣ በጤና፣ በወጣቶችና ግብርና ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል ያሉት አስተዳዳሪው፥ የልዩ ወረዳውን ተወላጆችና አጋሮች በየቦታዉ የማደራጀትና አባላት የማፍራት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ፣ ሀደሮና ሀዋሳ ከተሞች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን የማደራጀት ስራ መሰራቱን ጠቅሰዉ በዛሬዉ ዕለትም በዱራሜና ሆሳዕና ከተሞች ተመሳሳይ ተግባር እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በልዩ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞችና የልዩ ወረዳዉ አርሶ አደሮችን አባል በማድረግ ሀብት የማሰብሰብ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
የረጅም ጊዜ የልዩ ወረዳ መዋቅርን የለዉጡ መንግስት ምላሽ መስጠቱን የገለፁት የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪና የልማት ማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር ሀብታሙ በላይነህ፤ ልዩ ወረዳ መሆን ብቻዉን በቂ ባለመሆኑ ተወላጁ ባለበት ቦታ ሁሉ የልዩ ወረዳዉ ልማት ማህር አባል በመሆን የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቅዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ድልነሳዉ ታደሰ
More Stories
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም በክልሉ 8 ወረዳዎች በመንገድ ግንባታና ጥገና እንዲሁም ተንጠልጣይ ድልድይ፣ የተለያዩ የመንገድ ስትራክቸር ስራዎችን እየሰራ ይገኛል – መሀመድ ኑሪዬ (ዶ/ር)
ተመራቂ ተማሪዎች ስብእናን ተላብሰው እውነታን ይዘው ሀገሪዊ ራእይን ሊያሳኩ እንደሚገባ ተገለጸ
በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ሳውላ ካምፓስ 303 ተማሪዎችን አስመረቀ