ተመራቂ ተማሪዎች ስብእናን ተላብሰው እውነታን ይዘው ሀገሪዊ ራእይን ሊያሳኩ እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ተመራቂ ተማሪዎች ስብእናን ተላብሰው እውነታን ይዘው ሀገሪዊ ራእይን ሊያሳኩ እንደሚገባ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የቦርድ ሰብሳቢው እና የኢፌዴሪ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ፍሰሀ ይታገሱ ገለጹ፡፡
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ በዋናው ሚዛን ግቢ በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 638 ተማሪዎችን በድሀረ ምረቃ እና በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች አስመርቋል።
ዩኒቨርስቲው በዋናው ሚዛን ግቢ በዛሬው ቀን ለ17ኛ ጊዜ ያስመረቃቸው 638 ተማሪዎች በአራት ኮሌጆች እና በአንድ ትምህርት ቤት ትምህርታቸው ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎችን ናቸው።
በተማሪዎች ምረቃ ስነስረአት ላይ የተገኙት የዩኒቨርስቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር ዋቆ ገዳ እንደተናገሩት ዩኒቨርስቲው ባለፉት አመታት ከ40 ሺ በላይ ከተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የተወጣጡ ተማሪዎችን በድህረ ምረቃ እና በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች አስተምሮ ለፍሬ ያበቃ ዩኒቨርስቲ ነው ብለዋል።
ዩኒቨርስቲው ዛሬም ለ17 ኛ ጊዜ ማስመረቁንም የተናገሩት ዶክተር ዋቆ፥ ዩኒቨርስቲው በሶስት ኮሌጆች የመማር ማስተማር ሂደቱን በማከናወን የሀገሪቱን ፍላጎት ያገናዘቡ ትምህርቶች እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።
የመምህራንን ደረጃ ለማሳደግ ዩኒቨርስቲ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፥ የአከባቢው ማህበረሰብ የትምህርት ፍላጎት ለማሳካት እና ተደራሽ ከማድረግ አንጻርም ከሶስቱ ግቢ ባለፈ በአቅራቢያ በሚገኙ አጎራባች ከተሞች በቅዳሜ እና እሁድ ፕሮግራሞች ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
የአከባቢ ቋንቋ ለማሳደግም በሶስት የአከባቢ ቋንቋዎች በመጀመሪያ ዲግሪ የመማር ማስተማር ስራዎች እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።
በባለፉት ሶስት አመታት የመውጪያ ፈተና ከወሰዱት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ውስጥ ሰማኒያ ከመቶዎችን ማሳለፍ መቻሉን ጠቁመዋል ይህም ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ዶክተር ዋቆ ገዳ የተናገሩትም።
ዩኒቨርስቲው የህብረተሰቡን የትምህርት ፍላጎትን ለማሳደግ ለመጀመሪያ ጊዜ በ4 የትምህርት መስኮች የሶስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ከቀጣይ አመት ጀምሮ እንደሚጀምርም ጠቁመዋል።
ተማሪዎች የልፋታችሁን ውጤት ስላገኛችሁ መምህራኑም ተማሪዎችን አስተምራችሁ ለፍሬ በማብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል ዶክተር ዋቆ ገዳ።
ዩኒቨርስቲው ከመማር ማስተማር ስራ ባሻገርም የምርምር ስራዎችንም አጠናክሮ የማስቀጠል ስራ እንደሚሰራም ተናግረዋል ።
ተማሪዎች ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉም በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ህብረተሰቡን በቅንነት እና በታማኝነት ማገልገል ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል።
የኢፌዴሪ የኢንዱስትሪ ፓርኮችዋና ስራ አስፈጻሚ እና የዩኒቨርስቲው ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ፍሰሀ ይታገሱ በበኩላቸው መመረቅ የአንድ ሰው የህይወት አንዱ ምእራፍ በመሆኑ የዛሬ ተመራቂዎች ለሀገር ለወገን ለማገልገል ራእይ የምትሰንቁበት ቀን መሆን ይገባልም ብለዋል።
በስራ ህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ለመቋቋም ተመራቂ ተማሪዎች ከወዲሁ እራሳችሁን ማዘጋጀት አለባችሁም ብለዋል። ተመራቂ ተማሪዎች ስብእናን የተላበሳችሁ ለእውነት የቆማችሁ የሀገሪቱን ራእይ የምታሳኩ እንድትሆኑ አደራ እላለሁ ብለዋል።
ተመራቂ ተማሪዎችም የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ አምባሳደር እንድትሆኑ አደራ ማለት እፈልጋለሁ ያሉት ዶ/ር ፍስሃ፥ በዩኒቨርስቲው የተጀመሩ የሪፎርም እና የምርምር ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል።
በምረቃ ስነስረአት ላይ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተሸላሚ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው በርካታ ፈተናዎችን አልፈው ለዚሁ ክብር መብቃታቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረው በሰለጠኑበት የሙያ ዘርፍም ህብረተሰቡን በቅንነት ለማገልገልም ቃል ገብተዋል።
ዘጋቢ: አብዮት በቀለ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም በክልሉ 8 ወረዳዎች በመንገድ ግንባታና ጥገና እንዲሁም ተንጠልጣይ ድልድይ፣ የተለያዩ የመንገድ ስትራክቸር ስራዎችን እየሰራ ይገኛል – መሀመድ ኑሪዬ (ዶ/ር)
የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ልማት ለማጠናከር አንድነት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ሳውላ ካምፓስ 303 ተማሪዎችን አስመረቀ