በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ሳውላ ካምፓስ 303 ተማሪዎችን አስመረቀ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ሳውላ ካምፓስ ለስምንተኛ ጊዜ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 303 ተማሪዎችን አስመረቀ።
በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሳውላ ካምፓስ አስተባባሪ አቶ ዘለቀ ዶሳ ለ8ኛ ጊዜ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 303 ተማሪዎች ለምረቃ መብቃታቸውን በሪፖርታቸው አመላክተዋል።
ተመራቂዎቹ በመደበኛና በሳምንት መጨረሻ መርሐ-ግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከተመራቂዎቹ መካከል 277ቱ በመጀመሪያ ድግሪ ሲሆን 26ቱ በሁለተኛ ድግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ስለመሆናቸው አብራርተዋል።
ካምፓሱ በ2008 ዓ.ም ወደ ስራ ከገባበት አስከአሁን 2 ሺ 400 ተማሪዎች በካምፓሱ መመረቃቸው በምረቃ ወቅት ተገልጿል።
በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ 3 ሺ 189 ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል ብለዋል።
የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኢንጅነር አብደላ ከማል ተመራቂዎች፤ራሳቸውን ተወዳዳሪ በማድረግ ዘመኑ ከደረሰበት ቴክኖሎጂ ጋር እራሳቸውን በማዘመን የሕዝብና የሀገር ኃላፊነትን ለመወጣት መትጋት እንደሚገባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተመራቂዎች በተማሩበት የትምህርት ዘርፍ ለሐገራችን ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን ሊያበረክቱ እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ በክብር እንግደነት የተገኙት የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ባስተላለፉት መልዕክት ያደጉና የበለጸጉ ሀገራት መነሻቸው በትምህርት ዘርፉ ላይ ትኩረት ሰጥተው በመስራታቸው ነዉ ብለዋል።
ተመራቂ ተማሪዎችም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የቀሰሙትን ዕውቀት በተሰማሩበት የስራ መስክ በተግባር በመለወጥ አገራቸውን የሚጠቅም ስራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ተመራቂዎች በተማሩበት የትምህርት ዘርፍ ስራ ፈላጊ ሳይሆኑ ስራን በመፍጠር ለሐገራችን ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን ሊያበረክቱ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በምረቃ መርሐ ግብሩ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ምሩቃን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።።
ያነጋገርናቸው ተመራቂ ተማሪዎች በሰጡት አስተያየት በሰለጠኑበት ሙያ መስክ ስራ ፈጥረው ለመስራት እና ማህበረሰቡን በቅንነትና በታማኝነት ለመገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል::
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም በክልሉ 8 ወረዳዎች በመንገድ ግንባታና ጥገና እንዲሁም ተንጠልጣይ ድልድይ፣ የተለያዩ የመንገድ ስትራክቸር ስራዎችን እየሰራ ይገኛል – መሀመድ ኑሪዬ (ዶ/ር)
የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ልማት ለማጠናከር አንድነት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
ተመራቂ ተማሪዎች ስብእናን ተላብሰው እውነታን ይዘው ሀገሪዊ ራእይን ሊያሳኩ እንደሚገባ ተገለጸ