በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ ለ10ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 161 ተማሪዎች አስመረቀ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ ለ10ኛ ዙር በመደበኛና በኤክስቴንሽን መረሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን 161 ተማሪዎችን አስመረቀ።
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ ተማሪዎችን ባስመረቀበት ወቅት የዱራሜ ከምፓስ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ዘውዴ ክፍሌ ዩኒቨርስቲው 161 ተማሪዎችን ማስመረቁን ገልጸው፥ ካምፓሱ ከ1 ቢልዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን እያስገነባ መሆኑንም ተናግረዋል።
የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግር ለመፍታት ከ4 ሚልዮን በሚበልጥ ወጪ የመብራት ትራንስፎርሜር ገዝቶ መስጠቱን አቶ ዘዉዱ ገልጸዋል።
የዋቸሞ ዩኒቨርቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳዊት ሃዬሶ በበኩላቸው ካምፖሱ በ7 ዘርፎች የአእምሯዊ ንብረት ማረጋገጫ ማግኘቱን ጠቂመው፥ በቀጣይም በ2 ዘርፍ ተጨማሪ ለማግኘት ጥረት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ትምህርት ከግለሰብ አልፎ የህብረተሰቡን ችግር ፈቺ መሳሪያ በመሆኑ በተግባር ለመፈተን እራሳችሁን አዘጋጁ የሚል መልዕክትም አስተላልፏል።
ተመራቂዎች ያስተማራቸውን ህብረተሰብና ቤተሰብ ለማገዝ እንዲሁም ለሀገር ሰላም የራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡ ዶክተር ዳዊት አሳስበዋል።
የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ ስራ አመራር ቦርድ አባል አቶ አረገ እሸቱ ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲው ቆይታ በቀሰሙት እውቀት ሀገራቸውን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ መክረዋል።
ሀገራችን በከፍተኛ የለውጥ ጎዳና ላይ በምትገኝበት በዚህ ወቅት መመረቃችሁ ልዩ ያደርጋችኋል ሲሉም ጠቁመዋል::
የሀምበርቾ 777 ደረጃ ላይ እየተሰራ ያለውን የቱሪስት መስህብ የእለቱ ተመራቂዎች እንዲያስተዋውቁ ዋና አስተዳዳሪ ጥሪ አቅርበዋል።
ተመራቂ ተማሪዎች በሰጡት አስተያየት ለአመታት የለፉበትን ውጤት እና የድካማቸውን ፍሬ በመየት ለዛሬው ለምርቃት በመብቃታቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ያገኙት ክህሎትና እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር በተሰማሩበት የሙያ መስክ ሀገራቸውን ለማገልገል መዘጋጀታቸውን ጡቁመዋል።
ዘጋቢ: ታምሬ አበበ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የእምርታ ቀንን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት:-
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መልዕክት፡-