የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥርና ኳራንታይን ባለስልጣን ህገ-ወጥ የግብርና ግብዓት ዝውውርን ለመከላከል ከግብረ ሀይልና ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይ መድረክ እያካሄደ ይገኛል
ግብርናን ለማዘመን ጥራት ያለው ግብዓትን በማቅረብ በቴክኖሎጂ የመደገፍና ህገወጥ የግብዓት ዝውውርን የመከላከል ስራ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዑስማን ስሩር በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል።
መንግስት ግብርናን ለማዘመን ፖሊሲ በማሻሻል የግብርና መካናይዜሽን ከታክስ ነፃ እዲገባ ማድረጉንም ተናግረዋል።
የምርጥ ዘር አቅርቦትና ስርጭት ሰንሰለት እንዲያጥር እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
የምርጥ ዘር፣ የማዳበሪያ፣ የእንሰሳት መድሐኒት አቅርቦትና ስርጭት ላይ ከፍተኛ ሙስናና ህገ ወጥ የግብአት ዝውውር ያለበት በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ አቶ ዑስማን ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡ አበባ ሌንዲዶ
More Stories
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የእምርታ ቀንን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት:-
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መልዕክት፡-