የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ለ15ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 200 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው
ተመራቂ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በቀሰሙት እውቀት ማህበረሰባቸውንና ሀገራቸውን ለማገልገል የድርሻቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።
ተማሪዎቹ ታማኝ ስራ ወዳድ ታታሪና ከስሜታዊነት ይልቅ በምክንያታዊነት የሚያምኑ በስነ-ምግባር የታነጹ እንዲሁም ድህነትን የሚጸየፉ ሊሆኑ እንደሚገባ ተመላክቷል።
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሀገሪቱ የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት በርካታ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።
በመረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል እና የዩኒቪርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ አባል ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የተማሪ ወላጆች እየተሳተፉ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ አስቻለው አማረ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የእምርታ ቀንን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት:-
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መልዕክት፡-