የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ልማት በማፋጠን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሻሻል ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገለፀ
ከተማዋን ለማልማት ለሚደረገው ጥረት ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በጉራጌ ዞን የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱልቃድር ሂጅራ እንዳሉት ከተማ አስተዳደሩ ፈጣን ልማት በማረጋገጥ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሻሻል ዘርፋ ብዙ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል።
በበጀት ዓመቱ በከተማው ህብረተሰቡ ሲጠይቃቸው የነበሩ የመንገድ ከፈታ የጠጠር እና የጌጠኛ ድንጋይ ማንጠፍ እንዲሁም የጎርፍ ማፋሰሻዎችንና ሌሎች ተግባራት በጥራትና ፍጥነት በማከናወን ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል ያሉት ከንቲባው ፡፡ በአራቱም ቀበሌዎች ከ30 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ከፈታ ተግባር መከናወኑንም ጠቁመዋል ።
በከተማዋ ህበረተሰቡ በተደጋጋሚ የሚነሳው የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ውስንነት ለማሻሻል በመንግስት ከአርባ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ አንድ ጥልቅ የጉድጓድ ውሃ በማስቆፈር አገልገሎት እንዲሰጥ መደረጉን ገልጸው በዚህም የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋኑ ወደ አርባ ከመቶ እንዲያድግ አስችሎታል ብለዋል።
በጉንችሬ ከተማ በማዞሪያና ቆጭራ ቀበሌ ነዋሪዎች የሚነሳው የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከተማ አስተዳደሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት መፍትሄ ለመስጠት በመሰራት ላይ እንደሚገኝም አቶ አብዱልቃድር ተናግረዋል።
ወጣቶች በከተማው በግንባታ ፣በማንፋክቸሪንግ በከተማ ግብርናና ሌሎችም የስራ ዘርፎች ተደራጅተው በመስራት ተጠቃሚነታቸውን በማሳደግ ላይ እንደሚገኙ የተናገሩት ከንቲባው ከዚህ ቀደም የተሰራጨ የገንዘብ ብድር ተመላሽ እንዲደረግ በመስራት ለተጨማሪ የገንዘብ ብድር በማሰራጨት የስራ እድል ለመፍጠር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የወጣቱ የስራ ባህል ለማሻሻል የተለያዩ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስራዎች እተሰሩም ይገኛል ብለዋል።
በከተማዋ እያስተዋለው ባለው የልማት እንቅስቃሴ ደስተኛ እንደሆነ የገለጸው የጉንችሬ ከተማ ነዋሪ ሙባረክ ናስር ይህ ውጤት በከተማው አመራር ቅንጅትና ቁርጠኛነት የተገኘ እንደሆነና እንደነዋሪ ለከተማዋ ልማት መፋጠን አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ስለመሆኑም ተናግሯል።
ወጣት አያልቅበት ሰንብት በከተማው በግንባታ ዘርፍ ተደራጅተው እንዲሰሩ የስራ እድል ከተፈጠረላቸው ወጣቶች መካከል አንዱ ሲሆን በሰጠው አስተያየት ከስራ ባልደረቦቹ ጋር በጋራ የጌጠኛ ድንጋይ ማንጠፍ እና ጠጠር የማልበስ ተግባራት በጥራት በማከናውን ለከተማዋ ልማት መፋጠን የበኩላቸውን ኃላፊነት እየተወጡ እንደሚገኙ ጠቅሶ ሁሉም በየተሰማራበት የሙያ ዘርፍ ለከተማዋ እድገት አስተዋጾ ማበርከት እንደሚጠበቅበትም ጠቁሟል።
ዘጋቢ፦ ሪድዋን ሰፋ-ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
“አንድነታችንን በማጎልበት የህዝብ ጥቅም የሚያስቀድም ፖለቲካ ማራመድ ይጠበቅብናል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት መጠናከር መሰረት የሆነው ብዝሃነትን በአግባቡ የማስተናገድ ሂደት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገለፀ
በክረምቱ ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ