ሻምፒዮኑ የጊምቦ ዳዲበን ክለብ ዑፋ ከተማ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት
ሀዋሳ፡ ግንቦት 30/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ክልል በተካሄደው የክለቦች እግር ኳስ ውድድር ካፋ ዞንን በመወከል ሻምፒዮን የሆነው የጊምቦ ዳዲበን ክለብ ዑፋ ከተማ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡
ክለቡ ዑፋ ከተማ ሲደርስ መላው የተከማዋ ነዋሪዎች በደስታ ተቀብለውታል፡፡
የጊምቦ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ጥላሁን ለተጫዋቾችና የእንኳን ደስ ያላችው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ክለቡ ባስመዘገበው ውጤት ከፍተኛ ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡
የወረዳው አሰተዳደር ክለቡ በቀጣይ የተሻለ ውጤት እንዲያሰመዘግብ ያስችለው ዘንድ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
የክለቡ አምበል ኤፍሬም ምትኩ ቡድናዊ አንድነትና ጥንካሬ ለድል እንዳበቃቸው ተናግሯል፡፡
የቡድኑ አሰልጣኝ ፍጥነት መሸሻ በበኩሉ ቡድኑ ባሰመዘገበው ውጤት መደሰታቸውን ገልጸው ሰኔ 14 ቀን 2015 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የክለቦች ውድድር ላይ የተሻለ ውጤት ለማስመዘገብ እንደሚሰሩ ተናግሯል፡፡
ዘጋቢ፡ብዙአየሁ ጫካ- ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
ሮድሪጎ ቤንታንኩር ከእግር ኳስ ጨዋታዎች ታገደ
በቀቤና ልዩ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ 5ተኛ አመት ምስረታን ምክንያት በማድረግ ማህበረሰብ አቀፍ የማስ ስፖርት በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል
የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገ ጤናማና ንቁ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ