በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተካሄደው የክለቦች ውድድር ምርጥ ችሎታ ያላቸው ተጫዋቾች የታዩበት መሆኑ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ግንቦት 30/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ለመጀመሪያ ግዜ የተካሄደው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የክለቦች እግር ኳስ ውድድር ምርጥ ችሎታ ያላቸው ተጫዋቾች የታዩበት ነው ተባለ።

ክልሉ በቀጣይ በብሔራዊ ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ ሁኖ እንዲቀርብ ክለቦቹ ህዝባዊ መሠረት እንዲይዙ ሊሰራ እንደሚገባም ተጠቁሟል።

የመጀመሪው የክልሉ እግር ኳስ የክለቦች ውድድር በቦንጋ ከተማ ሲካሄድ ቆይቶ በካፋ ተወካዩ ጊንቦ ዳዲበን አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል።

በክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ውድድርና ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በየነ ቴቃ እንደገለጹት እንደ ክልል የመጀመሪያ ውድድር ቢሆንም ከየክለቦቹ ምርጥ ተጫዋቾች የታዩበት ውድድር እንደነበር ተናግረዋል።

እተጫዎቾች ከክልሉ አልፎ በሀገር አቀፍ ደረጃ መፎካከር የሚችሉ መሆናቸውን ያነሱት አቶ በየነ በኢትዮጵያ የሚገኙ ክለቦች ፍታቸውን ወደ ክልሉ ቢያዞሩ ውጤታማና ትርፋማ ይሆናሉ ብለዋል።

ሀዋሳ ለሚደረገው ሀገር አቀፍ የክለቦች ውድድር ብርቱ ተፎካካሪ ለመሆን ክልሉን የሚወክሉ ክለቦችም በአከባቢ ብቻ ሳይወሰኑ በክልሉ የሚገኙ ተጫዋቾችን በቡድናቸው እንዲያካትቱ ጠቁመዋል።

የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትል ሀላፊና የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አህመዲን አወል በበኩላቸው የአከባቢው ህዝብ ለስፖርት ያለው ፍቅር የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሁለት ክለቦችን የሚያሳትፍ ክልል እንደመሆኑ ይህ በክልልና በዞን መንግስት ወጪ ብቻ የሚቻል ባለመሆኑ ክለቦቹ ከመንግስት ድጋፍ ተላቀው ህዝባዊ መሠረት መያዝ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ክልሉ በሀገር አቀፍ ውድድር አራት ክለቦችን ለማሳተፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደረሽን ውሳኔን እየተጠባበቀ መሆኑም ተመላክቷል።

ዘጋቢ፡ ድንቃየሁ ዮሐንስ – ከቦንጋ ጣቢያችን