በክልሉ እየተስተዋለ ያለው ህገ-ወጥ የህጻናት የጉልበት ብዝበዛና ፍልሰት ዘርፈ ብዙ ችግር እያስከተለ ነው -አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር)
የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ገፅታና ተጋላጭነት ላይ የተደረገ ክልላዊ የዳሰሳ ጥናት ውጤት ላይ ያተኮረ ምክክር በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሂዷል።
በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ም/ርዕሰ መስተዳድርና ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ አበበየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እንደተናገሩት በክልሉ በህፃናት ላይ እየደረሰ ያለው ህገ-ወጥ የጉልበት ብዝበዛ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የሚገኝ በመሆኑ ባለ ድርሻ አካላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጡ ይገባል።
በክልሉ እየተስተዋለ ያለው ህገ – ወጥ የህጻናት የጉልበት ብዝበዛና ፍልሰት የህፃናትን የመማር እድላቸውን በመንፈግ ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች እየዳረጓቸው ስለመሆኑ የተናገሩት ም/ርዕሰ መስተዳደሩ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ማህበራዊ ተቋማት ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ዶ/ር አበባየሁ አያይዘውም የችግሩን አሳሳቢነትን በጊዜ ለመግታት የፍትህ ተቋማት በህ-ገወጥ የህፃናት ዝውውር ላይ የሚሳተፉ አካላት ላይ አስተማሪ የህግ ርምጃ በመውሰድ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባልም ብለዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ሳይቀር ህፃናት ጉልበታቸው እየተበዘበዘ መሆኑ ታውቆ በዘርፉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ማድረግ ይገባልም ብለዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ በበኩላቸው በክልሉ የሚስተዋለውን ህገወጥ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛና ዝውውርን ለመግታት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ስለ መሆኑም አመላክተዋል።
ዘጋቢ: በኃይሉ ሙሉጌታ

More Stories
በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ
የእናቶችንና ጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል