በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል የተመራ የአመራር ቡድን በቡታጅራ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎበኘ
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል የተመራ የአመራር ቡድን በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡
ቡድኑ የቡታጅራ ከተማ የኮሪደር ልማት፣ የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት እና የክላስተር ቢሮዎች ግንባታ አሁን ያለበትን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል።
በአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት እየተሰራ ያለው የቡታጅራ ከተማ የህዝብ ፋርማሲ 95 በመቶ መድረሱ ተመላክቷል።
የክልል ማዕከል ቢሮ ግንባታ መጓተቶች ቢኖሩትም አሁን ላይ ወደ ሰራ ተገብቶ በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ስለመሆኑ ተመላክቷል።
የኮሪደር ልማት ስራው በተያዘለት ዕቅድ እየሄደ መሆኑን የሱፐርቪዥን ቡድኑ ገምግሟል፡፡
በቡታጅራ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የከተማ ልማት ስራዎች ከተማዋ የለውጥ ጎዳና ላይ እንደምትገኝ አመላካች ነው ሲሉ አቶ ስንታየሁ በግብረ መልሳቸው አመላክተዋል።
ህብረተሰቡ በከተማ ልማት ስራዎች እያደረገ ያለው ተሳትፎ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት አቶ ስንታየሁ ይህን ተግባር ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አመላክተዋል።
የከተማ ልማት ስራዎች ዕውን እንዲሆኑ የማዘጋጃ ቤታዊ የገቢ አሰባሰብን ማዘመን አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ባዬ በልስቲ

More Stories
በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ
የእናቶችንና ጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል