የፈጠራ ውጤቶቹ ይበልጥ ውጤታማና ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ተደራሽ እንዲሆኑ የባለድርሻ አካላት ድጋፍና ተሳትፎ ወሳኝ ስለመሆኑም ተመላክቷል።
በጉራጌ ዞን የአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲንና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ መንግስቱ ብርሃኑ፤ በኮሌጁ እየተሰሩ ያሉ ጊዜና ጉልበት ቆጣቢ የፈጠራ ስራዎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የፈጠራ ስራዎችን በመስራትና የፈጠራ ሀሳብ ያላቸውን ግለሰቦች በመደገፍ ተቋሙ ለዘርፉ ውጤታማነት የበኩሉን ኃላፊነት እየተወጣ መሆኑን አስተባባሪው አስረድተዋል።
በእሴት ሰንሰለት፣ በፍላጎት ልየታና የሀገር በቀል እውቀቶችን መሠረት በማድረግ የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታና የስራ ባህል የሚያሻሽሉ ሳይንሳዊ ፈጠራዎችን ለመስራት ተቋሙ እያደረጋቸው ያሉ ጥረቶችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሜታል ማኑፋክቸሪንግ አሰልጣኝና የዘርፉ ተጠሪ አንዳምላክ ደነቀ በትምህርት ክፍሉ ከተሰሩ የፈጠራ ስራዎች መካከል የእንሰት መፋቂያ ማሽን አንዱ መሆኑና ማሽኑ እንሰት ለመፋቂያ ይወስድ የነበረውን ጊዜና ጉልበት በመቆጠብ ለህብረተሰቡ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ አስረድተዋል።
የፈጠራ ውጤቱ የበለጠ ውጤታማና ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በአግባቡ ተደራሽ እንዲሆን የባለድርሻ አካላት የጋራ ቅንጅታዊ ተሳትፎና እገዛ ያስፈልጋል የሚሉት መምህሩ፤ በተለይም ለማሽኑ መስሪያ የሚያስፈልጉ ግብአቶች እጥረት ለሂደቱ ተግዳሮት እየሆኑ ስለሚገኙ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አመላክተዋል።
የኮሌጁ ስትራክቸራል ኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት አሰልጣኝ ኪሩቤል አረጋ በበኩላቸው፤ ከትምህርት ክፍሉ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ለእርሻ አገልግሎት የሚውል አነስተኛ ትራክተር መስራታቸውን ገልፀዋል።
ትራክተሩ እንደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታና ወቅት የእርሻ ማሳዎችን ለማረስ አቅም እንዳኖረው ተደርጎ ስለመሠራቱ የጠቆሙት መምህሩ፤ ቴክኖሎጂው ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
የአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲንና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴሽን ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ መንግስቱ ብርሃኑ፤ በሂደቱ ተግዳሮት የፈጠሩትን የፋይናንስና የግብአት እጥረት እንዲሁም ሌሎች መሠል ችግሮችን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
ዘጋቢ፡ አስቻለው ተስፋዬ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
በኮሌጁ እየተሰሩ ያሉ ጊዜና ጉልበት ቆጣቢ የፈጠራ ስራዎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ መሆናቸውን የአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስታወቀ

More Stories
በቀቤና ልዩ ወረዳ ማህበረሰቡ በመንገድ መሰረተ ልማት ስራ እያደረገ ያለው ተሳትፎ የሚበረታታ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት – የልዩ ወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሳ ኢዶሳ
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከ”ኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደር” ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጋር በመተባበር በሀዲያ ለአምብቾ ጎዴ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ
በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳሰበ