ከተለያዩ ወረዳ፣ ከተማ አስተዳደር፣ ዞንና ክልል የተውጣጡ የነጋዴው ማህበረሰብ እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጉብኝትና ምልከታ አድርገዋል።
በቦንጋ ክላስተር ማዕከል ውስጥ እየተሰራ ያለው የሀኢት ዳቦና እንጀራ አምራችና አከፋፋይ የሥራ እንቅስቃሴ በተሳታፊዎች የተጎበኘ ሲሆን በተቋሙ አስተባባሪዎች ገለጻና ማብራሪያ ተደርጓል።
ሀኢት የዳቦና እንጀራ አምራችና አከፋፋይ ማህበር በቀን 200,000 ዳቦና 20 ሺህ እንጀራ ያመርታል ተብሏል።
በመቀጠልም የቅመማ ቅመም ማምረቻና ማከፋፈያም ጉብኝት ተደርጓል።
የቅመማ ቅመም ምርቶች ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያዎች በመላክ አካባቢን ከማስተዋወቅ ባለፈ ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ፋይዳው የላቀ እንደሆነም ተገልጿል።
በክላስተር ማዕከል እየተሰሩ ካሉት የሥራ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የእንጨትና የብሎከት ማምረቻ ሥራዎችም ተጎብኝተዋል።
የጉብኝቱ ተሣታፊዎችም ወደመጡበት አካባቢ ሲመለሱ ከጉብኝቱ ያገኙትን ተሞክሮ ተግባራዊ እንዲያደርጉ የኢኖቬሽንና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛው ጋግያብ አሳስበዋል።
በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የበጀትና የክትትል ድጋፍ በ7 ሺ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው የአረንጓዴ ፓርክና የኮርደር ልማት ጉብኝት ተደርጓል።
ዘጋቢ፡ መለሰ ገብሬ – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ23ኛ ዙር በተለያዩ የሙያ መስኮች በመደበኛና በማታ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 347 ተማሪዎችን አስመረቀ
በ2018 በጀት ዓመት የተቀመጡ ግቦችን በማሳካት የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል – አቶ ፍቅሬ አማን
ሚዲያን ለአዎንታዊ ነገር በመጠቀም ወጣቱ ሀገርን መገንባት አለበት – የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን