የህፃናት መብትና ደህንነት ተጠብቆ የነገ ሀገር ተረካቢ ለማድረግ የሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የጋራ ትብብር ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ
የክልሉ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ የአፍሪካ ህጻናት ቀንን ምክንያት በማድረግ ለከፍተኛ ችግር ተጋላጭ የሆኑ ህጻናትን ለመደገፍ ያለመ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ፤ በህፃናት ላይ የሚደርሰው ጾታዊ፣ ስነ-ልቦናዊና አካላዊ ጉዳቶችን ቀድሞ ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ነው የተናገሩት።
የህፃናት መብትና ደህንነታቸው ተጠብቆ የነገ ሀገር ተረካቢ ለማድረግ የሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የጋራ ትብብር ወሳኝ መሆኑን የቢሮ ኃላፊዋ ጠቁመዋል።
የመድረኩ ዋነኛ ዓላማ ለከፍተኛ ችግር ተጋላጭ የሆኑ ህጻናትን ለመደገፍ እንዲሁም በህጻናት ጥበቃ እና ጉዲፈቻ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመድረኩ የቢሮ ኃላፊዎች፣ የሁሉም ዞኖች ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሞዴል ዕድር መሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ፡ በቀለች ጌቾ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ ባለዉ 7ኛ ዙር መስራች ጉባኤ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) አቀራቢነት፡-