በየተቋማቱ በኤችአይቪ ኤድስ መከላከል ዙሪያ የሚፈጠሩ ግንዛቤዎችን በማሳደግ የበጀትና ተያያዥ ችግሮችን መፍታት ላይ ሊተኮር እንደሚገባ ተገለፀ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ ላሉ ለየተቋማቱ ፎካል ፐርሰን የስልጠናና ውይይት መድረክ በጂንካ ከተማ አካሂዷል።
ከተሳታፊዎቹ መካከል ወ/ሮ ሠራዊት ሰላቶ፣ አቶ ዘውዴ ባልቻና ሌሎችም በሰጡት አስተያየት ውይይቱ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን ያየንበትና ለቀጣይ ተግባር ግብዓት ያገኘንበት ስልጠናና ውይይት እንደሆነ ገልፀዋል።
አክለውም የኤች አይ ቪ ኤድስ ሥርጭት ተጋላጭነትን ለመቀነስ ከአመራሩ ትኩረት መስጠት ጀምሮ በተለያዩ መንገዶች በሚፈጠሩ የግንዛቤ ሥራዎች ለውጦች እየመጡ መሆኑን ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ በቀጣይ በዘርፉ ከስልጠና ጀምሮ የኮንዶም እጥረት፣ 0.5 የኤች አይ ቪ በጀት በኮድ በየተቋማቱ አለመሆንና አለመጠቀም፣ በባለቤትነት የክትትል ሥርዓት አለመጠናከርና ሌሎች ተያያዥ ችግሮችን በቅንጅት መፍታት ላይ ሊተኮር እንደሚገባ አንስተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና ዘርፈ ብዙ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማቲዎስ ጋርሾ፤ ሀገር በቀል የፋይናንስ ሥርዓትን በመከተል በኤች አይ ቪ ዘርፍ ከሰው ኃይል ጀምሮ የሜይንስትሪሚንግ ሥራዎችን ለማሳለጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ተነጋግሮ በቅንጅት በመፍታት በዳታ ሲስተም በመታገዝ የመረጃ ተዓማኒነትና ጥራትን መሠረት በማድረግ የሚስራ ይሆናል ብለዋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
በክረምት ወራት የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች ወጣቶች አልባሌ ስፍራ እንዳይውሉ ከማድረግ በተጓዳኝ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ምቹ እድል እየፈጠረ መሆኑ ተገለጸ
በአርሰናል እንደ አዲስ ብርሃን የፈነጠቀው ክርስቶስ ጾሊስ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ23ኛ ዙር በተለያዩ የሙያ መስኮች በመደበኛና በማታ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 347 ተማሪዎችን አስመረቀ