የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ህጋዊና አስተዳደራዊ ተጠቃሚነትን ለማሣለጥ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ
የቢሮው የወሳኝ ኩነት ዘርፍ፤ ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከተውጣጡ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት በክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ የጸጥታ ዘርፍ ምክትልና የወሳኝ ኩነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ደነቀ እንዳሉት፤ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ አስተዳደራዊና ህጋዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አይተኬ ሚና አለው።
በተለይ ፍርድ ቤቶች ከፍቺና ከጉዲፈቻ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ኩነቶች እንዲመዘገቡ የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በመድረኩ ከስድስቱ ዞኖች በተመረጡ ወረዳዎች የተደረጉ የድጋፍና ክትትል ግብረ-መልሶች ቀርበው ውይይት ተደርጓል።
ከተሳታፊዎች መካከል የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ቆጭቶ ገብረማርያም እና የካፋ ዞን ሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መዓዛ ሃይለማሪያም በሰጡት አስተያየት፤ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ስራው አንዲሣለጥ የበኩላቸውን አስተዋጾ አጠናክረው አንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
በመድረኩ የክልልና የዞን አመራሮች እንዲሁም ከስድስቱ ዞኖች የተውጣጡ የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ፡ መቅደስ ታደሠ – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
በክረምት ወራት የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች ወጣቶች አልባሌ ስፍራ እንዳይውሉ ከማድረግ በተጓዳኝ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ምቹ እድል እየፈጠረ መሆኑ ተገለጸ
በአርሰናል እንደ አዲስ ብርሃን የፈነጠቀው ክርስቶስ ጾሊስ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ23ኛ ዙር በተለያዩ የሙያ መስኮች በመደበኛና በማታ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 347 ተማሪዎችን አስመረቀ