ሀዋሳ፡ ግንቦት 21/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የተቀናጀ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሚዲያ መፍጠር ለሀገር ብልጽግና ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ ገ/መስቀል ጫላ ገለጹ፡፡
ሚዲያ በእውነትና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ተጨባጭ መረጃዎችን ለህዝቡ ተደራሽ ከማድረግ አኳያ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ተመላክቷል።
“የድህረ እውነት ዘመንን በእውነትና በእውቀት” በሚል መሪ ሀሳብ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለተወጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎችና አመራር አካላት በወላይታ ሶዶ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
ስልጠናውን ያስጀመሩት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፖርቲ ቅረንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል ጫላ በንግግራቸው “የተቀናጀ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሚዲያ መፍጠር ለሀገር ብልጽግና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
ሚዲያ በእውነትና በእውቀት የተመሰረተ ተጨባጭ መረጃዎችን ለህዝቡ ተደራሽ ከማድረግ አኳያም የበኩሉን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።
የውሽት ትርክት ለማጥፋት ሚዲያ ትልቅ ድረሻ አለው በማለት ሀገሪቱን በሰለጠነ መረጃ ለማበልፀግ ከዚህ ቀደም በተሰራው ሥራ ለውጥ መመዝገቡን ጠቁመዋል።
ህዝቡ ለሰላም፣ ለልማትና ለዴሞክራሲ በማነሳሳት በኩል ሚዲያ ከፍተኛ አስተዋዕጾ በማድረግ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን አክለዋል።
ሚዲያ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ከማጎልበት አኳያ ወቅቱን የሚመጥን መረጃ በማቅረብ በለውጡ ትሩፋት የተገኙ ውጤቶች በሚገባ ልክ ከማስተዋወቅ ረገድም ሀላፊነት መወጣት አለባቸው ብለዋል።
በድህረ እውነት ወቅት ላይ እንገኛለን ያሉት የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ ፈዲላ ቢያ ሚዲያ የህዝቦች ማህበራዊ መሰረት ለመገንባት ትልቅ ድረሻ አለው ብለዋል።
ሚዲያ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ጠቃሚና ትኩስ መረጃዎችን እንዲሁም ችግር ፈች የሆኑ መረጃዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
የስልጠናው ዋነኛው ዓላማ ከመረጃ ወቅታዊነት ጋር ተያይዘው ጠንካራ የሚዲያ ባለሙያዎችን መፍጠርና ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁ በማድረግ በቀጣይ ዓመታት አመርቂ ድሎችን ለማስመዝገብ መሆኑ ተጠቁሟል።
ዘጋቢ፡ በቀለች ጌቾ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ
የእናቶችንና ጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል