ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናወኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናወኑ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን በማስመልከት በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ “የኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ወንድሜ ኡሑሩ ኬንያታን የቴሌኮም ፍቃድ ስምምነትን በምንፈራረምበት በዛሬው ታሪካዊ ዕለት ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደኅና መጡ ለማለት እወዳለሁ” ብለዋል፡፡