ሀዋሳ፡ ግንቦት 25/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ዓመታዊ አገር አቀፍ የመመሰጋገንና የመደናነቅ ቀን በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው።
ፕሮግራሙ የተዘጋጀው የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና ቅን ኢትዮጵያ ማህበር ከተለያዩ ባለድርሻ አካለት ጋር በመተባበር ነው።
በፕሮግራሙ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃለፊዎች፣ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም የሙያ ማህበራት ተሳትፈዋል ።
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሁለት ዓመታት የመመሰጋገን ቀን ማክበሩ የሚታወስ ሲሆን የዘንድሮው ዓመታዊ የመመሰጋገንና የመደናነቅ ቀን “ተማሪዎች ለሀገር ሰላም ናቸው” በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ የሚገኘው።
ዘጋቢ፡ ጌታሁን አንጭሶ
More Stories
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም
ጃፓን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ብራዚልን አሸነፈች
ከተሞች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዘው አገልግሎት መሥጠታቸው የተገልጋይና የአገልጋይ ግንኙነት ጤናማና እርካታ የተሞላበት እንዲሆን የሚያስችል መሆኑ ተገለጸ