ሀዋሳ፡ ግንቦት 25/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የአማሮ ልዩ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት የበጎ ፈቃድ ሥራን ባህል ልናደርግ ይገባል ሲል አስታውቋል፡፡
በዘንድሮ ክረምት ለወጣቶች በጎ ፈቃድ ሥራ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ለመሆኑ ተጠቁሟል፡፡
የአማሮ ልዩ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳግም ጃምቦ፥ ለክረምት በጎ ፈቃድ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ኮሚቴ በማዋቀር ተቋማት የየራሳቸውን ዕቅድ እንዲያቀርቡ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ባለፈው ዓመት በ13 ዘርፎች ከ23 ሺህ በላይ ወጣቶች በተለያዩ በጎ ተግባራት የተሳተፉ ሲሆን በዘንድሮው ክረምት ሥራ ክልሉ በሚያቀርበው ዕቅድ መነሻ ለማሰማራት ዝግጅት መደርጉን ኃላፊው ገልጸዋል።
የአረጋውያንን ቤት ማደስ፣ የተበላሹ መንገዶችን መጠገን፣ ማዕድ ማጋራት ከአምናው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ሲሆኑ በዘንድሮው ክረምት ደግሞ ድጋፍ ለሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች ለመድረስ እና የተሻለ ለመሥራት መታሰቡ ተጠቁሟል።
የበጎ ፈቃድ ሥራ በክረምት ወቅት ለወጣቶች ብቻ የሚተው ባለመሆኑ፥ ሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሠራ እንደሆነና ህብረተሰቡ በጎ ሥራን ባህሉ ማድረግ እንዳለበት ነው አቶ ዳግም የገለፁት።
ከበጎ ፈቃድ ሥራው ባሻገር የክረምት ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና በተለየዩ የስፖርት ዓይነቶች እንደሚካሄድ እና የአማሮ ቡና የእግር ኳስ ክለብ እንደገና በማነቃቃት ወደ ቀድሞ አቋሙ የመመለስ ሥራ እንደሚሠራም ተመልክቷል።
ዘጋቢ፡ ለምለም ኦርሳ – ከፍስሃገነት ጣቢያችን

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)