ሀዋሳ፡ ግንቦት 02/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የባስኬቶ ዞን ተወላጆች የአንድነት መድረክ ማጠቃለያ “አንድነትና ህብረት ለባስኬቶ ከፍታና ለህዝቦች ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ውይይቱ ከተለያዩ ማህበራዊ መሠረቶች ጋር ሲካሄድ የቆየ መሆኑ ተመላክቷል።
በመድረኩ በፌደራልና በክልል በተለያየ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሚገኙ የባስኬቶ ዞን ተወላጆች፣ የባስኬቶ ዞን የሶስቱም መዋቅር የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል።
የባስኬቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ፍሬው ፍሻለው በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ህዝቡ እርስ በርስ ትስስር የሚፈጥርበት እና በአካባቢው እድገትና ልማቶች ዙሪያ በመግባባት ወደ ተግባር የሚገባበት ነው ብለዋል።
ለዘላቂ አንድነትና ህብረት መሠረት በመጣል ለላቀ ሥራ በቁጭት መቆም የሚያስችልና ተጨባጭ ለውጥ ለማስመዝገብ ያለመ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በመሆኑም አንድነትን ከሚሸረሽሩ አስተሳሰቦች በመራቅ በጋራ መተሳሰብ ላይ የጋራ ሥምምነት መፍጠር እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
በመድረኩ በዞኑ በሁሉም ማህበረሰብ ክፍሎች በየደረጃው የተካሄዱ ውይይቶች ዙሪያ የተዘጋጀ የማጠቃለያ ሰነድ ለውይይት ቀርቧል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
የህብረተሰቡን ጤና ለማጎልበት የዘርፉን ተግባራት በተገቢው ለማሳካት ከምንጊዜውም በተሻለ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
የህዝቡን የልማት ፍላጎቶች ለማሟላትና መንግስታዊ አገልግሎቶችን በተገቢው ለመስጠት የውስጥ ገቢ ግብርን አማጦ ለመሰብሰብ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ