የቡርጂ ዞን አስተዳደር፣ የዞኑ ሴቶችና ህጻናት ዩኒት፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ዩኒት እና የወጣቶች ክንፍ በሶያማ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት ስነ-ስርዓት አከናውነዋል።
የቡርጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳኜ ህዶ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ ድጋፍ የተደረገው በተለያዩ መስሪያ ቤቶች እንደሆነና ወጣቶች ማህበረሰቡን በማስተባበር ያደረጉት በመሆኑ ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ ብለዋል።
ለአቅመ ደካሞች በበዓል ወቅት ብቻ ሳይሆን በሌሎች ጊዜያትም ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፤ በቀጣይ በቋሚነት የሚደገፉበትና ስራ የሚያገኙበት አግባብ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የቡርጂ ዞን ሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወ/ሮ ማሪያም ሲሳይ፤ የተደረገው ድጋፍ ከጎናችሁ መሆናችንን ማሳያ ነው በማለት ይህም አንድነት እና አብሮነትን እንደሚያጠናክር አስረድተዋል።
በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን የገለጹት ወ/ሮ ወለተኪዳን ገ/እግዚአብሔር እና ወ/ሮ ታፈሰች ታደሰ፤ መንግስትና ህዝብ ከጎናቸው እንደሆኑ በማሳየታቸው አመስግነዋል።
አቶ ወየሳ ማሞ የሶያማ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ ከዚህ በፊት በርካታ ድጋፎች ሲደረጉላቸው መቆየቱን በማንሳት ለህክምና እንዲሁም በቋሚነት ስራ እንዲሰሩ የተመቻቸላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ዘጋቢ: አሀዱ አሸናፊ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ጉልህ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ
ቀልጣፋ የመንገድና ትራንስፖርት አገልግሎት በለለበት ልማትን ማሳለጥ የሚቻል ባለመሆኑ፣ የገጠር መንገድ