ክልሉ ከተደራጀ ጀምሮ በሁሉም መዋቅሮች በግብዓት አቅርቦት እና ተደራሽነት የተሻለ ተግባር መኖሩ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 27/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ክልሉ ከተደራጀ ጀምሮ በሁሉም መዋቅሮች በግብዓት አቅርቦት እና ተደራሽነት የተሻለ ተግባር መኖሩን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ገለፁ፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የስርዓተ ምግብ ግብዓቶች አጠቃቀምና ላልተገባ ዓላማ ማዋልን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተዘጋጀ የኦሬንቴሽንና ምክክር መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ ክልሉ ከተደራጀ ጀምሮ በሁሉም መዋቅሮች በግብዓት አቅርቦት እና ተደራሽነት የተሻለ ተግባር መኖሩን ጠቁመዉ በበጀት ዓመቱም ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የኢኮኖሚ ልዩ አማካሪ ጋር በመቀናጀት በንቅናቄ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።
ይሁን እንጂ አሰከአሁን እየተፈታተነ ያለውን ለህብረተሰቡ የሚሰጠው የአገልግሎት ጥራትና ሪፖርት ዙሪያ በቀጣይ ሰፊ ውይይት ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል አቶ ሳሙኤል።
በበጀት ዓመቱ አስከአሁን ባለው ሂደት ምግብ ላይ የተሻለ ቢሆንም በስርዓተ ምግብ ደረጃ ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር ችግሮችን ለይቶ መመካከር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
በመድረኩ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የስርዓተ ምግብ አገልግሎቶች የ8 ወራት ስራ አፈፃፀም ሪፖርተ እየተገመገመ ይገኛል።
በምክክሩ ላይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የርዕሰ መስተዳድሩ የኢኮኖሚ አማካሪ ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ በለው፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌን ጨምሮ የቢሮው እንዲሁም የዞንና ልዩ ወረዳ የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡ ተዘራ በቀለ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
8ኛው ሀገር በቀል ዕውቀቶች ለዘላቂ ሠላም በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የምርምር ዐውደ ጥናት በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል
የፌደራል እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የባስኬቶ ዞን ተወላጆች አንድነት እና ወንድማማችነት ማጠናከሪያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የአፈር ማዳበሪያ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተገለጸ