የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ አርሶ አደሩ በዘመናዊ የሜካናይዜሽን እርሻ እንዲሳተፍ እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
የኣሪ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታፈሰ ተስፋዬ ፤ በበልጉ እርሻ 48 ሺህ 190 ሄክታር መሬት በወቅታዊ ሰብሎች ለማልማት እንደታቀደ ገልፀው፤ ከታቀደው ሄክታር በላይ የእርሻ ስራ መከናወኑንና ከዝናቡ ዘግይቶ መጀመር ጋር ተያይዞ ከ30 ሺህ ሄክታር በላይ በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል።
አክለውም የተሻሻለ አሰራርን በመከተል የሜካናይዜሽን እርሻን መሰረት በማድረግ በትራክተር እርሻ ለማልማት ከታቀደው 500 ሄክታር መሬት ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 163 ሄክታር መሬት የለማ ሲሆን 158 ሄክታሩ ለዘር ብዜት ስራና ቀሪው ለምግብ ፍጆታ እንደሚውል ገልፀው፤ ለስራው የጂንካ ዩኒቨርስቲ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አለሙ አይለቴ በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማሩ ስራ ባሻገር አቅሙን ለማጎልበትና ማህበረሰቡን ለማገልገል የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየሰራ እንዳለ ገልፀዋል።
አክለውም አርሶ አደሩ በዘመናዊ የአስተራረስ ስርዓት በሜካናይዜሽን እርሻን በትራክተር እንዲያርሱ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
በደቡብ ኣሪ እና ባካ ዳውላ ኣሪ ወረዳ በጨለጎድና ባይፂማል ቀበሌ በበቆሎ ምርጥ ዘር ብዜት የተደራጁ አርሶ አደሮች፤ የተሰማሩበት የበቆሎ ምርጥ ዘር ብዜት የእርሻ ስራ በባህላዊ የአስተራረስ ስርዓት ረጅም ጊዜ እንደሚፈጅባቸው ጠቅሰው፤ አሁን ግን የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀረበላቸው የትራክተር የእርሻ ስራቸውን እንዳቀላጠፈላቸው ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ በናወርቅ መንግስቱ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የትምህርት ግበዓት መሟላት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 57 ሺህ 241 ተማሪዎች የ2017 ብሔራዊ ፈተናን ለመፈተን መመዝገባቸው ተገለፀ
ክልሉ ከተደራጀ ጀምሮ በሁሉም መዋቅሮች በግብዓት አቅርቦት እና ተደራሽነት የተሻለ ተግባር መኖሩ ተገለጸ