የ2017 የጋሞ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር በወንዶች እግር ኳስ ውድድር በዳራማሎ ወረዳ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
ከጋሞ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር ሲካሄድ በቆየው የዞኑ ልዩ ልዩ ስፖርት ሻምፒዮና በፍፃሜ መርሃግብር የዳራማሎ እግር ኳስ ቡድን የምዕራብ አባያ አቻውን በመለያ ምት 2 ለ 1 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት መሆን ችሏል፡፡
በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት የተጠናቀቀው ጨዋታ ፍፃሜ ባለማግነቱ በተሰጠው የመለያ ምት የዳራማሎ ወረዳ እግር ኳስ ቡድን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸናፊ ሆኗል።
በመጀመሪያው አጋማሽ በ17ኛው ደቂቃ ላይ የዳራማሎ ወረዳ ተጫዋች 7 ቁጥሩ ስሞን ሽታ የመጀመሪያዋን ኳስ ከመረብ አገናኝቷል።
በሁለቱም ክለቦች ጠንካራ ፉክክር የተደረገ ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ የምእራብ አባያ ወረዳ የክለቡን የመጀመሪያ ጎል በማስቆጠር አቻ መሆን ችሏል።
በጠቃላይ የዳራማሎ እግር ኳስ ቡድን የምዕራብ አባያ አቻውን በመለያ ምት 2 ለ 1 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት መሆን ችሏል፡፡
በጨዋታው የሁለቱም ክለቦች ግብ ጠባቂዎች በሚገርም ሁኔታ ኳስን ሲያመክኑ ታይተዋል።
በመጨረሻም የዳራማሎ ወረዳ ቡድን የጋሞ ዞን ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና በመሆኑ የወርቅ ሜዳልያና የዋንጫ ሽልማት ከክብር እንግዶች እጅ ተበርክቶለታል።
ዘጋቢ፡ ገነት መኮንን – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
የ2017 የጋሞ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር በወንዶች እግር ኳስ ውድድር በዳራማሎ ወረዳ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

More Stories
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች