የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ 6ኛ የምድብ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።
በሞሮኮ አል አብዲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ለዋልያዎቹ የማሸነፊያ ግቦችን በረከት ደስታ እና አቡበከር ናስር እያንዳንዳቸው 3 ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ ሀትሪክ ሰርተዋል።
በምድብ አንድ የመጀመሪያ ድሉን ያሳካው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ6 ነጥብ ከጊኒ ቢሳው በግብ ክፍያ በልጦ 4ኛ ደረጃን መያዝ ችሏል።
በምድብ ማጣሪያው 5ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው የጅቡቲ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ በ1 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች
በ800 ሜትር ሴቶች አትሌት ንግስት ጌታቸው የብር ሜዳልያ አስገኘች