4 ሺህ 972 የግብረገብ መምህራን ለመጀመሪያ ጊዜ ስልጠና ይሰጣቸዋል – አቶ አንተነህ ፈቃዱ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 26/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) 4 ሺህ 972 የግብረገብ መምህራን ለመጀመሪያ ጊዜ ስልጠና እንደሚሰጣቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ አስታወቁ።
በዚህ ዙሪያ መግለጫ የሰጡት ኃላፊው፤ የግብረገብ ትምህርት በክልሉ በ2016 ዓ.ም በይፋ መጀመሩን አብራርተዋል።
የግብረገብ ትምህርት የተማሪዎችን ስነ ምግባር በመቅረፅ ለቀጣይ ህይወታቸው መደላድል ስለሚሆን በዕውቀት የተመራ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ስለዚህም በክልሉ በሁሉም ማዕከላት 4 ሺህ 972 መምህራን የመማር ማስተማር ስልጠናውን ይወስዳሉ ብለዋል።
የግብረገብ ትምህርት ተማሪዎች ከመምህራን ጋር ለሚኖራቸው መልካም መስተጋብር ስለሚፈጥር ለዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ስልጠናው የግብረገብ ትምህርት መፅሀፍት ባዘጋጁ የዩኒቨርሲቲ መምህራን የሚሰጥ ሲሆን የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት መምህራን ተሳታፊ ይሆናሉ።
ዘጋቢ: ባዬ በልስቲ

More Stories
በክረምት የታየው የበጎ ተግባር ተሳትፎ በበጋ ወራትም በማስቀጠል ደጋፊ የሚሹ ወገኖችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።
የአካባቢ ብክለትን በመቀነስ ውብና ጽዱ አካባቢ ለመፍጠር የደን ልማትና ጥበቃን ማጠናከር እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ደንና አካባቢ ጥበቃ መምሪያ ገለጸ
ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ