በሀዲያ ዞን ምስራቅ ባዳዋቾ ወረዳ የበልግ ግብርና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 26/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ምስራቅ ባዳዋቾ ወረዳ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ አኒዮ የተመራ ልዑክ የበልግ ግብርና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት መርሃ ግብሩን አስጀምረዋል።
በመርሃ ግብሩ የዞኑና የምስራቅ ባዳዋቾ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው ያስጀመሩ ሲሆን በወረዳው እየተከናወኑ ያሉ የግብርና እና ሌሎች የልማት ተግባራት የመስክ ምልከታ እያደረጉ ይገኛል።
ዘጋቢ: ሳሙኤል መንታሞ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
በክረምት የታየው የበጎ ተግባር ተሳትፎ በበጋ ወራትም በማስቀጠል ደጋፊ የሚሹ ወገኖችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።
የአካባቢ ብክለትን በመቀነስ ውብና ጽዱ አካባቢ ለመፍጠር የደን ልማትና ጥበቃን ማጠናከር እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ደንና አካባቢ ጥበቃ መምሪያ ገለጸ
ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ