በከተማው የሚገኘው የ”መቴያ ማህበር” በደቡብ አፍሪካ ከተመሰረተው የቅንልቦች ማህበር ጋር በመተባበር ለአቅመ ደካማ ዜጎች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
በድጋፍ አሰጣጡ ወቅት የተገኙት የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ለይኩን ሱልዶሎ እንደተናገሩት፤ በአካባቢው ለሚኖሩ አቅመ ደካሞችና አረጋዊያን የተደረገው ድጋፍ ከመልካምነት የመነጨ በጎ ተግባር ነው።
በከተማው በተለያዩ በጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ የሚሳተፉ የወጣቶች ማህበራት በስራ የሚገለፅ አስታዋሽ ያጡ አረጋዊያንና አቅመ ደካሞችን በመርዳት እጅግ የሚያስመሰግን ተግባራትን እያከናወኑ መሆናቸውን አቶ ለይኩን ገልፀዋል።
በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የስራ እንቅስቃሴ ውጤታማ የተቀናጀ ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ የሚገልፁት ከንቲባው፤ ከራስ ይልቅ ለሌሎች ቅድሚያ የሚሰጥ ወጣት ትውልድ እየተፈጠረ እንዳለ አንስተዋል።
ወጣቶች በአካባቢያቸው ልማት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የበለፀገች የጋራ ሀገር ለመገንባት ሁሉአቀፍ አመለካከትና መከባበርን መላበስ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ በጎ ተግባራት ላይ በመሳተፍ የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ እንደሚገኙ የሚናገሩት የመቴያ ማህበር ወጣት አባላት፤ በደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው ቅንልቦች ማህበር ጋር በመተባበር ለአቅመ ደካማ አረጋዊያን ምግብ ነክ ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።
በቀጣይ ጊዜያትም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በተጠናከረ መልኩ መሰል ተግባራትን ለማከናወን ሰፊ ዕቅድ እንዳላቸው ወጣቶቹ ገልፀዋል።
ወ/ሮ አዳነች ሊሞሬና አቶ ዮሐንስ ጫፋሞ ድጋፍ ከተደረገላቸው አቅም ደካሞች መካከል ሲሆኑ በወጣቶቹ የተሰጣቸው የምግብ ቁሳቁስ በሚያስፈልጋቸው ወሳኝ ጊዜ የቀረበላቸው መሆኑን ጠቁመው፤ እንደዚህ ዓይነት መሰል በጎ ተግባራት በሌሎች አካላትም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስታውቀዋል።
ዘጋቢ: ዳኜ አየለ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶችን የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ለመቅረፍ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጎልበት የጤና አደረጃጀቶችን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግባት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እንደሚገባ መልዕክት ተላለፈ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ከ10 ቢልዮን ብር በላይ በጀት ለተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲውል በተገቢው እንደሚሠራ ገለፀ