ቢሮው “ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች” በሚል መሪ ቃል ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለማወዳደር ነው ያለመው ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ በዛብህ ገበየሁ እንዳሉት በክህሎት ፣ በቴክኖሎጂና በጥናትና ምርምር ሥራዎች ውድድር ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ተናግረዋል ።
በክልል ደረጃ ብቁ የሆኑ ተወዳዳሪዎች አልፈው በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚወዳደሩ ገልፀዋል ።
ይህ ውድድር በመካከለኛ የሰለጠነ የሰው ኃይል ከፍ ለማድረግና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ለማህበረሰቡ በማቅረብ ኑሮን ለማሻሻል ተልሞ የሚሠራ መሆኑን አክለዋል ።
በክህሎት ልማት በ20 ሙያዎች 61 ሰልጣኞች ፣ በሰልጣኝ 4 ክላስተር ፣ በአሰልጣኝ 6 ክላስተር እንዲሁም በእንተርፕራይዝ ደረጃ 14 ቴክኖሎጂዎች የሚቀርቡ ይሆናሉ ብለዋል ።
በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ሥራዎች የተጠኑ 6 የምርምር ውጤቶች ይቀርባሉ ፡፡
ዘጋቢ፡ሰሎሞን አላሶ-ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶችን የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ለመቅረፍ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጎልበት የጤና አደረጃጀቶችን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግባት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እንደሚገባ መልዕክት ተላለፈ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ከ10 ቢልዮን ብር በላይ በጀት ለተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲውል በተገቢው እንደሚሠራ ገለፀ