ሀዋሳ፡ መጋቢት 22/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) “የመጋቢታዊያን ፍሬዎች እና የነገ ተስፋዎች” በሚል መሪ ቃል በጌዴኦ ዞን የፐብሊክ ሰርቫንት ብልጽግና ፓርቲ ህብረት ውይይት ተካሂዷል፡፡
የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የመንግሥት ረዳት ተጠሪ አቶ ምህረቱ ተፈሪ እንዳሉት፤ ብልጽግና ፓርቲ በፈተናዎች መካከል ተወልዶ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል የለውጥ ፍሬ የተበሰረበት መጋቢት ወር ነው።
መጋቢት ወር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ወደ ሥልጣን የመጡት፣ ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብን በራስ አቅም ልጆቿን አስተባብራ መሥራት እንደምትችል ያረጋገጠችበትና ወደ ማጠቃለያ ምዕራፍ እንደደረሰች የጠቁሙት አቶ ምህረቱ፤ እነዚህ ሁነቶች የመጋቢታዊያን ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች መሆናቸውን አንስተዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ፈተናዎችን ወደ ዕድል ቀይረው በርካታ የመጋቢታዊያን ፍሬዎች በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤቶች የተመዘገቡት የነገ ተስፋዎች ማሳያ መሆናቸውን አብራርተዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ የመጋቢታዊያን ፍሬዎች አገርን የሚያሻግሩና ከፍ የሚያደርጉ ሥራዎች በሁሉም ዘርፎች እየተሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።
በዞኑ “የመጋቢታዊያን ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” በሚል መሪ ቃል በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ እና በአስተዳደር ዘርፎች እየተካሄዱ ባሉ ሦስቱም መድረኮች ላይ መነሻ የብልጽግና ፓርቲ ዕቅዶች ቀርበው በፐብሊክ ሰርቫንት የፓርቲ አባላት ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በውይይቱ አባላቱ ብልጽግና ፓርቲ የያዛቸው ዕቅዶች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ወሳኝ በመሆናቸው ለማሳለጥ በቁርጠኝነት መረባረብ ይገባል ብለዋል።
በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም እና በሌማት ትሩፋቶች እንዲሁም የኮሪደር ልማት ሥራዎችና ሌሎችም ዘርፎች ላይ ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ፐብሊክ ሰርቫንቱ ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ ተስፋዬ ጎበና – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ እና የአደረጃጀት ዘርፍ የ2018 በጀት አመት አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዕቅድ ዙሪያ በታርጫ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው
ኦሞ ባንክ ሳውላ ዲስትሪክት በ2018 በጀት ዓመት ከ86 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ቁጠባ ማስመዝገቡን ገለጸ
እየተካሔደ ያለው ሀገራዊ ምክክር በሀገሪቱ አንድነት እና ሠላም ለማስፈን ፋይዳው የጎላ መሆኑን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ