በባለብዙ ወገኖች የተቀናጀ ርብርብ የህዝቦች ወንድማማችነት እና የብዝሃነት እሴቶች የጎለበቱበት ሰላማዊ ክልል ተፈጥሯል – የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ
ሀዋሳ፣ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በባለብዙ ወገኖች የተቀናጀ ርብርብ የህዝቦች ወንድማማችነት እና የብዝሃነት እሴቶች የጎለበቱበት ሰላማዊ ክልል መፍጠር መቻሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥትሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ባለፉት ዓመታት በሰላም ግንባታ ዘርፍ በተከናወኑ ተግባራትና በተመዘገቡ ውጤቶች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል ።
እንደ ሀገር በመሰረታዊ የሰላም ግንባታ ዘርፍ የተደረጉ ማሻሻያዎች ህዝቡ ለሰላም እሴቶች ያለው ዕይታ እንዲቀየር አስተዋፅኦ ማድረጉን አቶ አንድነት አሸናፊ በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡
እንደ ቢሮ ኃላፊው ገለጻ የክልሉ አብዛኞቹ አካባቢዎች በሰላም እጦት ውስጥ በነበሩበት ሁኔታ ክልሉ መመስረቱን አስታውሰው ባለፉት ሶስት አመታት ከባለድርሻ አካላት በተጨማሪ የተለያዩ ወገኖችን ባሳተፈ መልኩ በተደረገው ርብርብ ቀድም ስል የነበረውን አሉታዊ ገፅታ መቀየር ተችሏል፡፡
ታጥቀው የሸፈቱና የህዝቡን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ ቡድኖችና ግለሰቦች የሰላም ጥሪን ተቀብለው ህዝቡን መቀላቀላቸውንም በመጥቀስ።
ችግር በነበረባቸው አካባቢዎች የነበሩ የግል እና የመንግስት ተቋማትን ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው መመለስ ተችሏል።
የቢሮ ሃላፊው በማብራሪያቸው እንዳመላከቱት በየደረጃው የተቀናጀ ርብርብ በመደረጉ በአሁን ወቅት ሰላም የተረጋገጠበት፣ የወንድማማችነት እና የብዝሃነት እሴቶች የጎለበቱበት ክልል ተፈጥሯል።
በክልሉ ለተረጋገጠው ስላም የማህበረሰቡ ታላላቆችና የሰላም አምባሳደሮች ሚና ላቅ ያለ እንደነበር የቢሮ ሃላፊው አስረድተዋል።
ውጤታማ የሆኑ ሀገር በቀል ልምዶችን በሁሉም አካባቢዎች በማስፋት የሰላምና የአብሮነት እሴቶች ግንባታ እንቅስቃሴን ማጠናከር በቀጣይ ትከረት የሚሰጥበት ነው ።
ዘጋቢ፡- ወንድሙ ካኪሎ ከማሻ ቅርንጫፍ
More Stories
ክልሉ ከተደራጀ ጀምሮ በሁሉም መዋቅሮች በግብዓት አቅርቦት እና ተደራሽነት የተሻለ ተግባር መኖሩ ተገለጸ
8ኛው ሀገር በቀል ዕውቀቶች ለዘላቂ ሠላም በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የምርምር ዐውደ ጥናት በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል
የፌደራል እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የባስኬቶ ዞን ተወላጆች አንድነት እና ወንድማማችነት ማጠናከሪያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል