ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድን መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው
ፖርቹጋላዊው ኮኮብ ክርስቲያኖ ከሀገሩ ብሔራዊ ቡድን ጋር በርካታ ጨዋታዎችን በማሸነፉ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ እውቅና ተሰጥቶታል።
የአምስት ጊዜ የባሎንዲኦር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከፖርቹጋል ጋር 132 ጨዋታዎችን በማሸነፍ በርካታ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን ያሸነፈ ቀዳሚው የአለማችን ተጫዋች በመሆኑ ነው እውቅና የተቸረው።
ይህም ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የተሰጠው አራተኛው እውቅና ሆኗል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከወራት በፊት 901 ጎሎችን በማስቆጠሩ ብዙ የኢንተርናሽናል ጎሎችን ያስቆጠረ ተጫዋች በሚል ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ እውቅና ማግኘቱ ይታወሳል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
2ኛው የየም ዞን ስፖርት ሻምፕዮና በሣጃ ከተማ እየተካሄደ ነው
የ2017 የጋሞ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር በወንዶች እግር ኳስ ውድድር በዳራማሎ ወረዳ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ