በክልሉ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የፀጥታ አካሉ በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገለፀ

በክልሉ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የፀጥታ አካሉ በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገለፀ

‎ቢሮው በክልሉ ለሚገኙ የሰላምና ፀጥታ መምሪያ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት በግጭት መከላከል፣ አፈታትና በሰላም ባህል ግንባታ እንዲሁም በግጭት ማስተዳደርና አፈታት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአርባምንጭ እየሰጠ ይገኛል።

‎”ሠላማችንን በሰላሙ ጊዜ እንስራ” በሚል መሪ ቃል እየተሰጠ በሚገኘው ስልጠና ተገኝው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ተወካይ እና የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አንቄ እንዳሉት፤ ስልጠናው በክልሉ በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የግጭት ችግሮችንና አዝማሚያዎችን በመረዳት የሰላም ባህልን ለመገንባት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።

‎አክለውም ከስልጠናው ጎን ለጎን ሰላምና ፀጥታ፣ ፖሊስና ሚሊሽያ የክልሉ ማህበረሰብ በሰላም ወጥቶ በሰላም እንዲገባ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት ውይይት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበው ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና መልካም አስተዳደርን በክልሉ ለማስፈን በቅንጅት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

‎ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠው ስልጠና ለቀጣይ ስራ የሚያነሳሳና አሳታፊ እንደሚሆን እምነታቸው መሆኑት አቶ አዲሱ ተናግረዋል።

‎በስልጠናው በክልሉ የሚገኙ የፖሊስ፣ የሚሊሺያ ዘርፍ ኃላፊዎች፣ የግጭት አፈታት ዘርፍ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

‎ዘጋቢ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጫ ጣቢያችን