በፍጥነት እየተለዋወጠ የሚገኘዉን ዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታን በመረዳት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ መስራት ይገባል – ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር)
ሀዋሳ፡ መጋቢት 15/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በፍጥነት እየተለዋወጠ የሚገኘዉን ዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታን በመረዳት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ መስራት እንደሚገባ በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር) ገለፁ።
“ዉጤታማ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ለገዢ ትርክት ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ከክልሉ አመራር አካዳሚ ጋር በመተባበር ለሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በወልቂጤ ከተማ መስጠት ጀምሯል።
በፍጥነት እየተለዋወጠ የሚገኘዉን ዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታን በመረዳት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ መስራት እንደሚገባ የገለፁት በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር)፤ ለሚዲያ ስራ የሚቀረፁ አጀንዳዎች ለክልላዊና ሀገራዊ ሰላምና አንድነት እንዲሁም ሀገራዊ ግንባታን መነሻ ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል።
የሚዲያ ጥቅም የሚወሰነዉ እንደአጠቃቀሙ በመሆኑ ዘመኑን በዋጀ መንገድ አዉቆ መጠቀም ይገባል ያሉት ኃላፊዉ፤ በዚሁ መንገድ አክራሪነትንና ጽንፈኝነትን መታገል እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
በዘመነ በይነ መረብ ያለዉን ሚዲያ በመረዳት ገዢ ትርክትን ለማስረጽ ሚዲያ ትልቅ መሳሪያ መሆኑን የገለፁት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቱ፤ ይህን ታሳቢ በማድረግ ስልጠናዉ እየተሰጠ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ለስልጠናዉ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የተናገሩት የአካዳሚዉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ፤ አካዳሚዉ ለሁለንተናዊ ብልጽግና የሚተጉ አመራሮችን ለማብቃት ስልጠናዎችን ይሰጣል ብለዋል።
በመጀመሪያዉ ቀን ስልጠና “ኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ለእምርታዊ ዕድገት” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ በብልጽግና ፓርቲ ዓለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) እየተሰጠ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ድልነሳው ታደሰ
More Stories
የፍትህ ተቋማት ተገልጋዩን ህብረተሰብ በሚመጥን መልኩ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ ገለፁ
በተገልጋይ እርካታና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ የፍትህ ትራንስፎርሜሽንና የፍርድ ቤቶች ጥምረት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገለጸ
የዜጎችን ህይወት በማቀራረብ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ ከሚረዱ ጉዳዮች አንዱ የበጎ ፈቃድ ሥራ መሆኑ ተጠቆመ