በ800 ሜትር ሴቶች አትሌት ንግስት ጌታቸው የብር ሜዳልያ አስገኘች
ሀዋሳ: መጋቢት 14/2017 (ደሬቴድ) በ20ኛው የናንጂንግ ዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አትሌት ንግስት ጌታቸው ለኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አስገኝታለች።
አትሌት ንግስት ጌታቸው ውድድሩን 1 ደቂቃ ከ59 ሴኮንድ ከ63 ማይክሮሴኮንድ በሆነ ሰዓት 2ኛ ደረጃ ይዛ በማጠናቀቅ በሻምፒዮናው ለኢትዮጵያ 3ኛውን የብር ሜዳልያ አስገኝታለች።
የባለፈው ዓመት የርቀቱ አሸናፊ አትሌት ፅጌ ድጉማ 6ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ቼልሲ በሰንደርላንድ ሲሸነፍ ኒውካስል ፉልሃምን አሸነፈ
በሮዱዋ ደርቢ ሲዳማ ቡና ሀዋሳ ከነማን አሸነፈ
ሊቨርፑል፣ ቼልሲ፣ ሪያል ማድሪድና ባየርን ሙኒክ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ