ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት አሸነፉ
ሀዋሳ: መጋቢት 14/2017 (ደሬቴድ) በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በሴቶች 1500 ሜትር ፍፃሜ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ እና ደርቢ ወልተጂ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።
ውድድሩን የርቀቱ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነችው አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ 3 ደቂቃ ከ54 ሴኮንድ የሻምፒዮናው ክብረወሰን በሆነ ሰዓት በአንደኝነት አጠናቃ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ አስገኝታለች።
እንዲሁም አትሌት ድርቤ ወልተጂ 2ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ለሃገሯ የብር ሜዳልያ አስገኝታለች።
በዚህም ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው በ2 የወርቅ እና 2 የብር ሜዳልያዎች ከዓለም 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ሀገራችንን ወደ ብልፅግና ለማድረስ የጽናት መንፈሳችንን ማደስ እንደሚገባ ተገለጸ
“ትንንሽ የሚመስሉ ስራዎች ለትልልቅ ዕድሎች በር ይከፍታሉ” – ወይዘሮ ህልውና ጌታቸው
የህግ ታራሚዎችን በስነ ምግባር ለማነፅ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ገለፀ