የዳውሮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 26ኛ መደበኛ ጉባኤ በታርጫ ከተማ እየካሄደ ነው
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ዳዊት ሚኖታ እንደገለፁት፤ ምክር ቤቶች የወከላቸውን ህዝብ ጥቅም ለማስከበር በአስፈፃሚ አካላት የታቀደውን ልማት እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች በትክክል ገምግሞ አቅጣጫ ማስቀመጥ ነው።
ሪፖርቱን ያቀረቡት የዞኑ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፀሐይ አየለ፤ ምክር ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና የመንግሰት አሰራር ውሰጥ የህዝብ ተሳትፎን በማረጋገጥ በህብረተሰቡ ኑሮ ላይ አዎንታዊ ለውጥና እምርታ እንዲሁም መልካም አሰተዳደር እንዲሰፍን የሚሰሩ ተግባራት የተቋሙ ዓላማ መሆኑን በሪፖርታቸው አንስተዋል።
በቀረበው ሰነድ ላይ በትምህርት ቤቶች አፈፃፀም፣ በማዳበሪያ አቅርቦት እና የእዳ አመላለስ፣ ከኦዲት ግኝት በሚታዩ ችግሮችና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ የምክር ቤት አባላት አስተያየትና ጥያቄ በማንሳት ውይይት እየተደረገ ነው።
ጉባኤው በሚኖረው ቆይታ የምክር ቤትና የዞን አስተዳደር አስፈፃሚ ተቋማት እንዲሁም የፍርድ ቤት የ2017 በጀት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን በመገምገም የተለያዩ ሹመቶችን እንደሚያፀድቅም ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል።
ዘጋቢ፡ አንዱዓለም ኡማ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
የተገኘው አንፃራዊ ሰላም የእርስ በርስ ግንኙነቶችን ከማጠናከር ባለፈ ለረጅም አመታት በፀጥታ ችግር ያለማውን የማዕድን ሀብት በመጠቀም የአካባቢውን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በማጂ ወረዳ የሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ
በአካል ጉዳተኝነት ተስፋ ባለመቁረጥ የተገኘ ስኬት
ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ የውስጥ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ