በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት 19ኛው ዓመታዊ የቲቢ ምርምር ጉባኤ እና የ2017 የዓለም የቲቢ ቀን እየተከበረ ነው
ሀዋሳ፡ መጋቢት 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ‘በርግጥም ቲቢን መግታት እንችላለን፤ ቃል በተግባር ሐብት ለውጤት’ በሚል መሪ ቃል በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት 19ኛው ዓመታዊ የቲቢ ምርምር ጉባኤ እና የ2017 ዓ.ም የዓለም የቲቢ ቀን እየተከበረ ይገኛል።
በመድረኩ የጤና ሚኒስቴር ደኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገሪቱ ክልሎች የተጋበዙ እንግዶች እና ተመራማሪዎች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅት ተወካዮች በመሣተፍ ላይ ናቸው።
በመድረኩ ቲቢን የተመለከቱ የምርምር ሥራዎች እና የተለያዩ ዝግጅቶች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የየም ብሔር የ2019 የዘመን መለወጫ “ሄቦ” በዓል በዞኑ ሳጃ ከተማ እየተከበረ ይገኛል
የሀገራችንን የኢኮኖሚ አቅም ለማሳደግ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ማሟላት ወሳኝ በመሆኑ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ
“የዲጂታል አጀንዳ እና ሰው ሰራሽ አሰተውሎት ለቱሪዝም አዲስ ቅኝት” በሚል መሪ ቃል የቱሪዝም ቀን በጎፋ እና በወላይታ ዞኖች በድምቀት ተከብሯል