አጀንዳዎችን በማሰባሰብ የህዝቡ ጥያቄ በተገቢው እንዲመለስ የምክክሩ ሂደቱ የላቀ አስተዋፅኦ እንዳለው ተሳታፊዎች ገለፁ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) አጀንዳዎችን በማሰባሰብ የህዝቡ ጥያቄ በተገቢው እንዲመለስ የምክክሩ ሂደቱ የላቀ አስተዋፅኦ እንዳለው ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እየተካሄደ ያለው የአጀንዳ አሰባሰብና ተወካይ መረጣ መቀጠሉን የምክክር ኮሚሽኑ የክልሎች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር እና ዲያስፖራ አስተባባሪ አስታውቀዋል።
የምክክር ሂደቱን አስመልክተው አስተያየት የሰጡን የጌዴኦ ዞን ተሳታፊ መምህር አስራት እሸቱ እና የጎፋ ዞን ተሳታፊ መቶ አለቃ ተፈሪ ጤናው እንደ ሀገር የሚስተዋሉ ችግሮችን ለይቶ በሰለጠነ መንገድ መወያየት እና መፍትሄ መፈለግ ይገባል ብለዋል።
መንግስትም የህዝቡን አጀንዳ በመቀበል የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በተገቢው በመመለስ ግጭቶች እንዳይፈጠሩ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ያሉት ተሳታፊዎቹ የተሻለችውን ኢትዮጵያ ለመገንባት ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርአትን ማጎልበት እና ባህላዊ ሸንጎዎችን ማስፋፋት ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ምክክር ኮሚሽን የ7ቱ ክልሎች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እና የዲያስፖራ አስተባባሪ አቶ ረታ ጌራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ2 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የአጀንዳ አሰባሰብና የተወካይ መረጣ እያካሄዱ መሆኑን ጠቁመዋል።
በቀጣይ ቀናትም ተፅእኖ ፈጣሪ እና ታዋቂ ሰዎች እንዲሁም የመንግስት አካላት እና የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚመክሩበት እና አጀንዳ የሚመርጡ መሆኑን አስታውቀዋል።
በደቡብ ኢትዮጰያ የምክክር እና የአጀንዳ መረጣ ሂደት ያለምንም ችግር እየተካሄደ መሆኑን የገለፁት አቶ ረታ በክልሉ የሚደረገው ሂደት የተሳካ እንዲሆን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ላበረከው አስተዋፅኦ በኮሚሽኑ ስም አመስግነዋል።
በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተደረገ ያለው የምክክ ሂደት በቀጣይ 3 ተከታታይ ቀናት እንደሚቀጥልም ተመላክቷል።
ዘጋቢ ፡ ገነት መኮንን – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 32ኛ የምክር ቤቶች የጋራ ምክክር ፎረም እያካሄደ ነው
የላስካ ከተማ ነዋሪዎችን የመሠረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
የፈጠራ ስራ አዳዲስ ሀሳቦችንና እውቀቶችን በተግባር ላይ በማዋል ወደሚጨበጥ ኢኮኖሚ ለመቀየር ፋይዳው የጎላ መሆኑን በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት አስታወቀ