የጂንካ ዩኒቨርስቲ  ለኤሶል ልዩ አዳሪ ትምህርት የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ

የጂንካ ዩኒቨርስቲ ለኤሶል ልዩ አዳሪ ትምህርት የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ

ዩኒቨርስቲው ከመማር ማስተማር ጎን ለጎ የማህበረሰብ አገልግሎት ተደራሽነት በማስፋት የትምህርት ጥራትንና የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ ለውጥ በሚያሳድጉ የልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት አድረጎ እየሰራ ነው ።

በርክክብ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አምባ ጩፋ ዩኒቨርስቲው የትምህርት ጥራትን ለማሻሻልና የማህበረሰብ አቅፍ አገልግሎት የማጠናከር ሥራ እየሰራ መሆኑን ገለጸው በአሁኑ ድጋፍ ለአዳሪ ትምህርት ቤት በገንዘብ ሲተመን ከ360 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸውን የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያችን ማለትም ኮምፒውተሮችን የማባዣ ማሽኖች እንዲሁም የመኝታ ፍራሾችንና ትራንሶች የውሃ ሮቶዎችን ዩኒቨርስቲው ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል ።

ድጋፉን የተረከቡት የኤሶል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ አዝመራ ውድነህ ለድጋፉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የጂንካ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ተወካይና የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት አለሙ አይላቴ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ግዴታውን ለመወጣት እየተጋ ነው ብለዋል ፡፡

ምክትል ፕረዚዳንቱ አክለው ለኤሶል ልዩ አዳሪ ት/ቤትከቁሳቁስ ድጋፍ በተጨማሪ ለትምህርት ቤቱ መምህራን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተሻለ ዕውቀትና ችሎታ እንዲኖራቸው ዩኒቨርስቲው ይደግፋል ሲሉ ተናግረዋል ።

ዘጋቢ ፡ ጄታ ታገሠ – ከጂንካ ጣቢያችን