የዛሬ ስራችን ቤታችን ያፈራውን እርድ ጨምሮ ሌሎችን ለተቸገሩ ወገኖች ማካፈል ነው – ሃጂ ሙፍቲ እድሪስ

በአዲስ አበባ ስቴዴየም እስልምና እምነት ተከታዮች የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልን በድምቀት እያከበሩ የሚገኙ ሲሆን፥ በበዓሉ ሃይማኖት አባቶች እና ምዕመናን ተገኝተዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር ኢድሪስ ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸውም የዛሬ ስራችን ቤታችን ያፈራውን እርድን ጨምሮ ሌሎችን በማካፈል የምናስታውሰው ነው ብለዋል፡፡ በስነ ስርዓቱ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ሃላፊ አቶ ጥራቱ በየነም ለህዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡