የአሪ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምስረታ እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ የካቲት 06/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የአሪ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምስረታ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሐጂ ያሲን ከድርን ጨምር የአሪ ዞን አስተዳደር ተወካይን፣ የዞንና የጂንካ ከተማ አስተዳደር የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
የአሪ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ማታዶ በርቢ የሚመሰረተው ምክር ቤት ለሠላምና አንድነት ትልቅ ፈይዳ እንዳለው ገልፀዋል።
የአሪ ዞን ዋና አስተዳደር ተወካይ አቶ ተመስገን ተረፈ የህዝቡ ሠላምና ልማት እንዲረጋገጥም የድርሻውን የሚያበረክት ይሆናል ብለዋል፡፡
የህዝቦችን አንድነት እንዲጠናከር ያግዛል ያግዛል ያሉት ደግሞ የአሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ምክትል አፈጉ ባኤ አቶ ሲሳይ ጋልሺ ናቸው።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ-ከጂንካ ቅርንጫፍ

More Stories
አቶ ይሁን አሰፋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
አቶ መብራቴ ወልደማርያ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ያስገነባቸውን 100 መኖሪያ ቤቶችን ለኮንሶ ዞን ተፈናቃዮች በይፋ አስተላለፈ