በሃገሪቱ የተወዘፉ ችግሮችን በመቅረፍ ወደ ምንዳ ለመቀየር በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ

ሀዋሳ፡ የካቲት 04/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሃገሪቱ የተወዘፉ ችግሮችን በመቅረፍ ወደ ምንዳ ለመቀየር በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ በምክትል ርእሰ መስተዳደር ማዕረግ የመሰረተልማት ክላስተር አስተባባሪና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር መሃመድ ኑሪዬ ገልፀዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለወልቂጤ ክላስተር የመንግስት ሰራተኞች “ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ቃል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

“ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ቃል በወልቂጤ ክላስተር ለሚገኙ የክልል የመንግስት ሰራተኞች የሚሰጠውን ስልጠና ያስጀመሩት ዶክተር መሃመድ ኑሪዬ ሃገሪቱ የተወዘፉ ችግሮች አሉባት ብለዋል።

በመሆኑም እነዚህ የተወዘፉ ችግሮችን ቀርፎ ወደ ምንዳ ለመቀየር በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም ነው የተናገሩት።

ሃብት መፍጠር እና ስልጡን ሲቪል ሰርቫንት መገንባት ላይ የሚያተኩረው ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ መሆኑንም ከመርሃ-ግብሩ ለማወቅ ተችሏል።

በስልጠናው በምክትል ርእሰ መስተዳደር ማእረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር መሃመድ ኑሪዬ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ መነቴ ሙንዲኖ፣ የወልቂጤ ክላስተር የቢሮ ሃላፊዎችና የመንግስት ሰራተኞች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡ አማን ቢካ – ወልቂጤ ጣቢያችን