በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ከሚሰሩ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር የሚመክር የትብብርና የአጋርነት ብሄራዊ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው
የምክክር መድረኩን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጀው።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ የምክክር መድረኩን በይፋ ሲያስጀምሩ እንዳሉት የምክክሩ ዓላማ በዘርፉ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በንጹህ መጠጥ ውሃ፣ በታዳሽና ዘላቂነት ባላቸው የኃይል አማራጮች በትብብርና በቅንጅት የሚያከናውኗቸውን ተግባራት በግልጽ ማወቅ ነው።
በእነዚህ መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት የተሠሩ ፕሮጀክቶችን የአስተዳደር ሥርዓት ማበጀትና በዘርፉ ያላቸውን አበርክቶ ዘላቂነትና ቀጣይነት እንዲኖራቸው የሚያደርጉ የትብብር ማዕቀፍ መዘርጋት ሌላኛው የትኩረት አጀንደ መሆኑን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዘውን ሀብት ማሰባሰብ የሚቻልበትን የጋራ ማዕቀፍ መዘርጋት ሌላኛው የምክክር መድረኩ ዓላማ መሆኑንሞ ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ አስታውቀዋል።
አሁናዊ የብሄራዊ መጠጥ ውሃ ሽፋን 68 ከመቶ በላይ እንደሚገኝም በዚሁ ጊዜ ጠቁመዋል።
በምክክር መድረኩ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክትል ዳይሬክተርን ጨምሮ በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የሚሠሩ የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተገኝተዋል።
በዘርፉ በአምስት ክልሎች ውስጥ የተሠሩ ሥራዎች ሪፖርት በሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ በአቶ አበራ እንደሻው ቀርቧል።
ሪፖርቱን ተከትሎ ውጤታማ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ ጌታሁን አንጭሶ
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ