የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ አስተዳደር የዞን እስልምና ምክር ቤት ምስረታ ጉባኤ የቡርጂ ዞን እስልምና ምክር ቤት የአባላት፣ ፕሬዝዳንትና ሥራ አሰፈፃሚዎችን አስመረጠ
የተመረጡ የምክር ቤቱ አባላት እና ሥራ አስፈፃሚዎች በቁራን እና በሀዲስ መሠረት ከመንግስት ጋር ሆነው ህዝበ ሙስሊሙን ለማገልገል ቃለመሃላ ፈፅመዋል።
በጉባኤው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሶያማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አቶ ሉላ አየለ እንደገለፁት የሁሉም ሃይማኖቶች መሠረት ፍቅር፣ ወንድማማችነት እና ሰላም በመሆኑ ሙስሊሙ ህብረተሰብ በአከባቢው ያሉ ቅራኔዎችን ለመፍታት ተባብሮ መሥራት ይገባቸዋል ብለዋል።
የቡርጂ ዞን አስተዳዳሪ ተወካይ እና የፀጥታ እና ሰላም መምሪያ ኃላፊ አቶ እስራኤል ገብሬ በበኩላቸው በደቡብ ክልል ቀደምት እስልምናን ከተቀበሉት ህዝቦች ተጠቃሿ ቡርጂ ዞን የተለያዩ የሀይማኖት ተከታዮች የሚኖሩበት ምድር ናት ብለዋል።
ቡርጂ ዞን ለኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም መስህብ የሚሆን መሬት ያላት ስትሆን ህዝበ ሙስሊሙ የአከባቢ ፀጥታ እና ሠላም ላይ ከመንግስት ጋር ሆኖ ሲሠራ የቆየ በመሆኑ መንግስት ለጉባኤው ስኬት አስፈላጊ ድጋፍ ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል።
የዞኑ መንግስት ተጠሪ አቶ አብድልቃድር ሁሴን የሙስሊሙ ህዝብ አሁን ከተመረጡ የዞኑ የእስልምና ጉዳዮች ምክርቤት አባላት እና ከሥራ አስፈፃሚዎች ጋር በጋራ መሥራት አለበት በማለት አብዛኛውን የሙስሊሙን ህዝብ መንግስ አብሮ ለመሥራት ዝግጁ ነው ሲሉ ተናግሮዋል።
ጉባኤው የቡርጂ ዞን እስልምና ምክር ቤት አባላትን፣ ሥራ አስፈፃሚዎችንና የወጣቶች እና የሴቶች ሊግ በሙሉ ድምፅ በመምረጥ ቃለመሃላ እንዲፈፅሙ አድርጓል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክርቤት ፕሬዝዳንት ሀጅ ያሲን ከድር በበኩላቸው ዛሬ የተመረጡት የዞኑ እስልምና ምክርቤት አባላት፣ የሥራ አስፈፃሚዎች፣ የወጣቶች እና የሴቶች ሊግ ሥራ አስፈፃሚዎች በሀይማኖቱ ብቃት እና እውቀት መሠረት የተመረጡ ናቸው በማለት አስረድተዋል።
የዞኑ እስልምና ፍርድቤት ቃድ ሸክ አብዱልወሃብ መሐመድ የተመረጡ የምክርቤት አባላትም ሆኑ ሥራ አስፈፃሚዎች ያለ አድሎ ለሙስሊሙ መሥራት አለባቹ ብለዋል።
ዘጋቢ: አብዶ አያላ – ከይርጋጨፈ ጣቢያችን
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ