ሀዋሳ፡ ጥር 29/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሁሉም አከባቢዎች በመካሄድ ላይ የነበረው የብልፅግና ፓርቲ የሴትና የወጣት ሊጎች የማጠቃለያ መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።
የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች በሀገራዊና ክልላዊ እንዲሁም በአከባቢያዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ጥልቅና ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
መሻሻልና ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸውን ጉዳዮችን አንስተዋል በስፋት መክረዋል።
ሴቶችና ወጣቶች በአመራር ቦታ እንዲመደቡ እንዲሁም ወጣቶችና ሴቶች እራሳቸውን እንዲያበቁ ሀሳብ ቀርቧል።
የክልሉ ህብረተሰብ አብዛኛው ወጣት ስለመሆኑ ተሳታፊዎቹ በማንሳት ወጣቱ ወደ ተሳሳተ መስመር እንዳይገባ የስራ ዕድል መፍጠር የቅድሚያ ቅድሚያ እንዲሰጠው ጥያቄ ቀርበዋል።
በሀገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች የሚከሰቱ የሰላም እጦቶች አሉታዊ ውጤታቸው ሁሉንም አከባቢዎች እያዳረሰ በመሆኑ ለሰላም ሁሉም በጋራ እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል።
በተለያዩ አከባቢዎች የተጀመሩ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክትቶች በተያዘላቸው መርሃግብር መጠናቀቅ ባለመቻላቸው የቅሬታ ምንጭ እየሆኑ በመሆኑ በጊዜ መፍትሄ እንዲሰጠው ሀሳባቸውን አጋርተዋል።
ዘጋቢ፡ ጀማል የሱፍ
More Stories
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ መመረቅን ምክንያት በማድረግ የይርጋጨፌ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር በጋራ በመሆን የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ
ሙያዊ ስነ-ምግባር የተላበሰ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ
የካፋ ዞን ጤና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 ዕቅድ ዝግጅት ላይ ውይይት እያካሄደ ነው