ሀዋሳ፡ ጥር 29/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ የተጀመሩ የንፁህ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ ።
በደቡብ ኢትዮጵያዊ ክልል በ15 ከተሞች የንፁህ መጠጥ ውሀ ግንባታ እንዲሁም በሶዶና አርባምንጭ ከተሞች የሳኒቴሽን ግንባታ እየተከናወነ እንደሚገኝ የክልሉ ውሀ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ጠቁሟል ።
በሪፖርቱ በግማሽ ዓመት ውስጥ የክልሉን ህዝብ የመጠጥ ውሀ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸው በማዕድን ልየታ ፣ በጌጣጌጥ ማዕድናት ማምረት ላይ ለተሰማሩ ማህበራት የገበያ ትስስር መፈጠሩ ተገልጿል ።
በግማሽ ዓመት ውስጥ በመደበኛ፣ ካፒታል ፣በኤስዲጂ ፣ በአሃዳዊ ዋሽ ፣ ኮዋሽ ፣ በዩኒሴፍ እና በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ አከባቢዎች በገጠር 14 የውሀ ተቋማትን በከተማ ደግሞ 3 የውሀ ተቋማትን በመገንባት 41 ሺህ 440 ህዝብንን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ።
በአማራጭ ኢነርጂ ፣ በማዕድን ሀብት ጥናት ፣ የውሃ ተቋማት ዘለቄታዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ ፣ የአደጋ ስጋት ዝግጁነት የቅድመ ዳሰሳ ጥናት ፣ ድጋፍና ክትትል ማድረግ መቻሉን በሪፓርቱ ቀርቧል ።
በክልሉ በገጠርና በከተማ የንፁህ መጠጥ ውሀ ሽፋን 52 በመቶ መድረሱን በሪፓርቱ ተመላክቷል ።
በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ የማብራሪያ ጥያቄዎች ከቋሚ ኮሚቴው ተሰንዝሮ ከመድኩ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል ።
በፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ የውጪ ምንዛሬ ጫና እንደፈጠረ የጠቆሙት የክልሉ ውሀ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ የሚገጥሙ ችግሮችን በቀጣይ ለመፍታት በቅንጅት እንደሚሰራ አብራርተዋል ።
የከተሞችን የውሀ አቅም እንዲያድግ ከግብረ ሰናይ ድርጅቶችና በህብረተሰቡ ተሳትፎ በዘላቂነት ለመፍታት ይሰራል ሲሉ ጠቁመዋል ።
የሶላር ቴክኖሎጂና የማዕድን ልማት እድገት በክልሉ እንደሚስተዋል ኢንጂነር አክሊሉ ጠቁመው ዋነኛ የቢሮው ችግር በጀት መሆኑንም አብራርተዋ ።
ችግሩን ለመቅረፍ በቀጣይ እንደሚሰራ ገልጸዋል ።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጠንክር ጤንካ በቀጣይ የህብረተሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሀ ፍላጎት ለማሟላት የተጀመሩ አበረታች ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል ።
ዘጋቢ ፡ ተመኙህ ገረሱ- ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ