ሀዋሳ፡ ጥር 29/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የፍትህ ሚኒስቴር በአዲሱ የፍትህ ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአርባምንጭ እያካሔደ ነው።
የፍትህ ማሻሻያው፥ የፍትህ ተቋማት ነጻና ገለልተኛ ሆነው እንዲሠሩ ያግዛልም ተብሏል።
ፍኖተ ካርታውን ቀድመው ተግባራዊ ባደረጉ አካባቢዎች የተሻለ ውጤት መመዝገቡን የፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ አቃቤ ህግ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ቃባ ተናግረዋል።
የፍትህ ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ቀደም ሲል በስራ ላይ የነበረው የፍትህ ስርዓት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ፣ ግልጽነት እና ተጠያቅነትን ይበልጥ በማስፈን የተገልጋይን እርካታ ለመጨመር ያግዛል ያሉት በፍትህ ሚኒስቴር የሪፎርም ዘርፍ ሚኒስቴር ደኤታ ዶ/ር ኤርሚያስ የማነ ብርሐን ናቸው።
በመድረኩ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕረሬዝዳንት አቶ ቦጋለ ፈይሳን ጨምሮ የፍትህ ተቋማት ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።
ዘጋቢ፡ ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
አቶ ይሁን አሰፋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
አቶ መብራቴ ወልደማርያ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ያስገነባቸውን 100 መኖሪያ ቤቶችን ለኮንሶ ዞን ተፈናቃዮች በይፋ አስተላለፈ